Ethiopian Maritime Authority

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን

ሁለተኛው ምዕራፍ የሎጂስቲክ ማስተር ኘላን የጥናት ሪፓርት በባለድርሻ አካላት ተገመገመ::

ሰኔ 22፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ሁለተኛውን የሎጂስቲክስ  ማስተር ኘላን ጥናት ሪፓርትን በባለድርሻ አካላት አስገምግሟል። 

በመርሃ ግብሩ ላይ ጥናቱን የሚያጠናው  አጥኝ  ድርጅት( ePtisa ) የሎጂስቲክስ ስርዓቱን የተሳለጠ ለማድረግ እና ወጪን እና ጊዜን በመቀነስ የአገሪቱን የሎጂስቲክስ አፈፃፀም ( LPI) ለማሻሻል  የአገሪቱን የንግድ ሁኔታ፣የሎጂስቲክስ ፍሲሊቲዎች ፣ የፍሬይት ትራንስፓርት ሞዶች ላይ የሚታዩ  ችግሮችን በመለየት ለእያንዳንዱ  የመፍትሔ ሀሳብ አመላክተዋል።

በቀረበው የጥናት ሪፓርት ላይ  ውይይት የተደረገበት ሲሆን በባለድርሻ አካላት በኩል ጥናቱ የአገሪቱ የሎጂስቲክስ ማስተር ኘላን እንደመሆኑ መጠን  ከዚህ ቀደም በሌሎች አካላት የተሰሩ ጥናቶችን ማካተት ቢችል፤ አዲሴ ከመገንባት ይልቅ  በስራ ላይ  ያሉትን መሰረተ ልማቶች መጠቀም ላይ ትኩረት ቢሰጠው የሚሉትን እና ሌሎች ጥያቄ እና አስተያየቶችም ተሰጥቶባቸዋል። አጥኝው ድርጅት አብዛኛው የተሰጡ አስተያየቶችን እንደግብዓት እንደሚወስዱ ገልፀው ማብራሪያ በሚሹት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ ጥናቱን ያቀረበውን ድርጅት እና ባለድርሻ አካላትን አመሰግነው፤ እያዘጋጀን ያለነው  የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ማስተር ኘላን እንደመሆኑ በሰነዱ ላይ የሚካተቱ ጉዳዮች በሚቀጥሉት ዓመታትን በመተንበይ እና ታሳቢ በማድረግ ሊቀመጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ሌላው በውይይት ወቅት  በባለድርሻ አካላት የተነሱትን አስተያየቶች በጥናቱ ውስጥ በማካተት እንዲሁም ስትራቴጂው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስለሚጠይቅ የግል ዘርፉን ለማሳተፍ ምን አይነት የማስተዋወቅ ስትራቴጂ ብንጠቀም ይሻላል የሚለውንም እንዲካተት አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *