ሰኔ10 ፣2018 ዓ.ም ( ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የማኔጅመንት አባላት የውስጥ አስራርን በማዘመን አሰራሩን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማቅረብ እና የአገልግሎት እንግልት ለማቃለል የሚረዳ እንደሆነ የታመነበትን የማሪታይም እና ሎጂስቲክስ ማኔጅመንት ሲስተም የኢንሰኘሽን ሪፓርት ገምግመዋል።
የኢንሰኘሽን ሪፓርቱን ሲስተሙን የሚያለማው (TRIA) የተባለው የግል ድርጅት ያቀረበ ሲሆን ኘሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ከአልሚው ድርጅት እና ከተጠቃሚው ድርጅት ምን ይጠበቃል፤ የሲስተም ልዩ ሰነድ፣ የስራ መከወኛ ዕቅድ እንዲሁም አጠቃላይ ስለኘሮጀክቱ አፈጻጸም እና ይዘት ለባለስልጣኑ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ሌላው አልሚው ድርጅት ኘሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ( በስድስት ወራት) ለማጠናቀቅ እና ከተጠናቀቀም በኋላ ሲስተሙ ውጤታማ እንዲሆን እገዛቸው እንደማይለያቸው ቃል ገብቷል።
በቀረበው የኘሮጀክቱ የኢንሰኘሽን ሪፓርት ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የባለስልጣኑ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላትም መተግበሪያው የውስጥ አሰራርን ከማቀላጠፉ አንጻር ከፍተኛ ተፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዳለው በማስረዳት ቢካተቱ ያሏቸውን ሀሳቦች ያስቀመጡ ሲሆን በተጨማሪም ለኘሮጀክቱ መሳካት ተገቢውን ድጋፍና ግብዓት በቁርጠኝነት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ፍራኦል ጣፋ:- የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ባለሥልጣኑ አገልግሎቱን ለማዘመን እና ተደራሽ ለማድረግ ዲጂታላይዝ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው ከዚህ ቀደም በማሪታይም ዘርፉ ላይ እየተሰጡ ያሉትን የዲጂታል ስራዎች አበልጻጊው እንደግብዓት መጠቀም እንደሚችል ገልፀዋል። አቶ ፍራኦል አያይዘውም አልሚው ድርጅት አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ከቴክኒካል ኮሚቴው ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥ ሲስተሙን በተቻለ አቅም በተያዘለት የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ እንዲችሉ አሳስበው የፕሮጀክት ትግበራው በተለየ መልኩ ክትትል የሚደረግበትና በባለስልጣኑ የበላይ አመራር ጭምር ክፍተኛ ድጋፍ እንደሚደረግ በማስመዝገብ የኢንሰኘሽን ሪፓርቱን ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።













Leave a Reply