Ethiopian Maritime Authority

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች   ስነ ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ላይ ስልጠና ወሰዱ

ሚያዝያ 15፣2018 ( ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስነ ምግባራዊ  ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ላይ ስልጠና ወስደዋል።

አቶ ፍራኦል ጣፋ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር የስልጠናው ዓላማ በባለሥልጣኑ ውስጥ የጥቅም ግጭትን በማስወገድ  በውሳኔ አሰጣጥ ሂደታችን ከእኛ ፈቅ ባለመልኩ  ስነምግባራዊ ውሳኔዎችን ለመወሰን የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናውን ከፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመጡ ታደሰ ወ/ሰንበት ( ዶ/ር ) የተሰጠ ሲሆን በዋናነት የጥቅም ግጭት ምንነት፤የተቋማት የጥቅም ግጭት ስጋትና ተጋላጭነት፤ የጥቅም ግጭት አይነቶች፤ የጥቅም ግጭትን መከላከል እና ማስወገድ ፤ የጥቅም ግጭት እና ሙስና ፤ የዘርፎች የወል የጥቅም ግጭት ስጋትና  ተጋላጭነት ላይ በተመለከተ ስልጠናውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ወ/ሮ ሶፍያ አልማሙን የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ሀላፊ ስልጠናው
ወቅቱን የጠበቀ እና አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው  ስልጠናው  ስለ ጥቅም ግጭት እና የአፈታት መንገዶች ላይ የተሻለ ግንዛቤን የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር    ውሳኔዎችን ስንወስን ከጥቅም ግጭት ወጥቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

በስልጠናው ላይ ከፌዴራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽንእና  ከተጠሪ ተቋማት ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *