
የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት የምረቃ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም (ትሎሚ)፡- የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ቀልጣፋና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የሎጂስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥ እውን ለማድረግ የሚያስችል የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት የማስመረቂያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የዲጂታል አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማዘመንና አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለትም ከአርቴፊፋል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር የለማውን የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት (IFTMS) በይፋ እያስመረቀ ይገኛል፡፡
ይህ የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት (IFTMS) ከአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቱት ጋር በትብብር የለማ ሲሆን የጭነት ትራንስፖርት የኦፕሬተርነት ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን ከተሸከርካሪና አሽከርካሪ መረጃ ጋር በማቀናጀት ለማስተዳደር ያስችላል፡፡
በተጨማሪም ስርዓቱ የተሸከርካሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችንና የረዳቶች የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ አሰጣጥን በማቀናጀት ሁኔታ ለመስጠት የሚያሥችልና የጭነት ትራንስፖርትን ዘርፍ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሠረታዊነት ሊፈታ የሚችል ስርዓት ነው፡፡
Source: EMA Official Telegram