Ethiopian Maritime Authority

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የዘመናዊ  የላብራቶሪ አገልግሎት ማቋቋሚያ ጥናት ረቂቅ ሪፓርት  ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ

ግንቦት 27፣2018 ዓ.ም ( ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የዘመናዊ ላብራቶሪ አገልግሎት ማቋቋሚያ ጥናት ሪፓርት   ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት  አደርጓል።

በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወርቁ ለማ ሎጂስቲክስ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በመሆኑ እና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ ባለሥልጣኑ የአስር ዓመት የብሔራዊ ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ በማዘጋጀት  በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ገልፀው የዚህ ስትራቴጂ አካል የሆነው የዘመናዊ ላብራቶሪ አገልግሎት ማቋቋም አንዱ መሆኑንና በተዘጋጀው የጥናት  ሪፓርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ ማስፈለጉን ገልፀዋል።

አቶ ወርቁ አያይዘውም የዘመናዊ ላብራቶሪ አገልግሎት መኖር በደረቅ ወደቦች አካባቢ አስተማማኝ ቀልጣፍ እና ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለመዘርጋት ችግሩን በጥናት ለይቶ ለተግባሪ አካላት ማሳየትና ለመፍትሔው ደግሞ ከስራው ባለቤቶች ጋር በጋራ መስራት አገራዊ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆን አብራርተዋል።

ጥናቱን ያጠናው  QAFRICA JV. INDIGO QUALITY MANAGEMENT CONSULTANCY ሲሆን በጥናት ሪፓርቱ ላይ የዘመናዊ ላብራቶሪ አገልግሎት በደረቅ ወደቦች አካባቢ ለማቋቋም በሎጂስቲክስ ዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን በመለየት የመጀመሪያ  እና ሁለተኛ ዳታዎችን የመሰብሰብ ስራ እንደተከናወነ፤ የሚታዩ ችግሮችን እንዲሁም የመፍትሔ ሀሳቦችን ተመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *