ሰኔ 20፣ 2018 ዓ.ም. (ኢማባ) – የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በ13ኛው የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ለመወዳደር ባቀረበው ማመልከቻ መሠረት፣ ከኢትዮጵያ ጥራት ድርጅት (EQA) በመጡ የግምገማ ባለሙያዎች የተካሄደውን የስራ ቦታ ላይ ግምገማ (On-site Assessment) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
የግምገማው ሂደት ቀደም ሲል በባለሥልጣኑ የቀረቡ ሰነዶችና ማስረጃዎች ላይ በተደረገው የሰነድ ግምገማ ውጤት መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ የEQA ባለሙያዎች በተቋሙ በመገኘት የአሠራር ሥርዓቶችን፣ የአፈጻጸም ማስረጃዎችን እና የጥራት አስተዳደር ትግበራዎችን በዝርዝር ገምግመዋል።

በግምገማው መዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ ቀደም ሲል የISO 9001፡2015 የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የምስክር ወረቀት በማግኘት አገልግሎቶቹን በዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርት መሠረት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በ13ኛው የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ሂደት መሳተፉም የተቋሙን የአፈጻጸም ደረጃ በተጨባጭ ለመለካትና የማሻሻያ አቅጣጫዎችን ለመለየት አስፈላጊ እድል እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ፍራኦል በተጨማሪም፣ የግምገማው ዋና ዓላማ ለሽልማት ብቻ መወዳደር ሳይሆን፣ የተቋሙን የጥራት አስተዳደር አፈጻጸም በገለልተኛ አካል እንዲገመገም፣ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች እንዲጠናከሩ እና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ተለይተው በቀጣይ ዘላቂ መሻሻል (Continual Improvement) እንዲመዘገብ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለሥልጣኑም ከግምገማው የሚገኙ ግብረመልሶችና ምክረ ሃሳቦችን በመተግበር የአገልግሎት ጥራቱን፣ የተቋማዊ አፈጻጸሙን እና የተገልጋዮች እርካታን በቀጣይነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት እንደሚያከናውን ተገልጿል።














Leave a Reply