የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል መደበኛ ስበሰባውን ያካሄደ ሲሆን የተለያዩ የጥናት ሰነዶችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ፡፡
ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑትን እና እስካሁን በኮሚሽኑ በኩል የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ ሰነድ ለውይይት ከቀረቡ ሰነዶች መካከል አንድ ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ለዘርፉ ቅድሚያ በመስጠት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አሰራርን በመዝርጋት እየሰራ መሆኑን በሰነዱ የተገለጸ ሲሆን በዋናነት አምራች ኢንዱስትሪው እድገት እንዳይፋጠን እንቅፋት የሆኑትን እና አምራቾች የሚያነሷቸውን መሰረታዊ ችግሮች በትክክል በመለየት ምቹ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ የካውንስሉ ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ ተናገረዋል ።

በዋናነት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያነሷቸውን መሰረታዊ ችግሮች በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል የገለጹት አምባሳደር ግርማ እንዴት፣መቼ እና በማን ችግሮቹ ይፈታሉ የሚለው ላይ ያተኮረ ሰነድ በማዘጋጀት ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም አክለዋል፡፡

አምራቾች ቀልጣፋና ምቹ እንዲሁም የአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ህጎችን እና መመሪያዎችን እንዲሻሻሉ ማድረግ፣የአሰራር ስርዓቱን አምራቾች እንዲያውቁት ማድረግ እና ሌሎች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ምቹ አሰራሮችን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሆነም በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል፡፡
በእለቱ የጥጥ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያኮረ የዳሰሳ ጥናትም ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡













Leave a Reply