የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ይህን የገለፁት ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ጋር የሚሰሩ፤
በጅቡቲ እና ኢትዮጵያ የሚገኙ የጉምሩክ አስተላላፊዎች፣ የመርከብ ወኪል ድርጅቶችና ትራንዚተሮች ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዘርፉ ተዋናዮች ያከናወኗቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል።
በገቢና ወጪ ጭነቶች የሚጠየቁ ሰነዶችን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አለመከወን፣ ወጥነት ያለው የሥራ ሰዓት አለመኖር፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚደረግ ጥረት ውስን መሆኑ ተብራርቷል።
የጭነት ሠነዶች በተገቢው መንገድ ተሟልተው ባለመቅረባቸው እና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ጭነቶች ባለመነሳታቸው የባቡር ጭነት ጉዞ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈ እንደሚገኝ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ የተቀናጀ አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ በመግለፅ ኢዲአር ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ በበኩላቸው በማሪታይም ዘርፉ መንግስት ያስቀመጣቸው ስታንዳርዶች መኖራቸውን ጠቁመው የመርከብ ወኪሎችና የጭነት አስተላላፊዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።
አቶ ፍራኦል ዘርፉ የሚገጥሙትን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በመገንዘብ ተጨማሪ የስታንዳርድ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎቹ መድረኩ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በተነሱ ክፍተቶችና ውስንነቶች ላይ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ከመድረኩ ጠቃሚ ግብአቶች መገኘታቸውን በመግለፅ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የግምሩክ አስተላለፊዎች፣ ትራንዚተሮችና የመርከብ ወኪል ድርጅቶች በሎጂስቲክ ዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን በመገንዘብ በላቀ ትጋት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አስተማማኝ የሥራ ትስስር መፍጠር፣ ጠንካራ የእርስበርስ መተማመንን ማጎልበት፣ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመንና መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያመቻቸውን ዕድል አልቆ መጠቀም እንደሚገባ በመግለፅ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር





Leave a Reply