ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ብረታ ብረቶች፣ ጣውላ እና መሠል ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል ሴንትራል ቢም ዋገን (Central Beam Wagons) – የባቡር ፉርጎ ወደ ስራ ገባ
ለበርካታ ዓመታት ያለሥራ ቆመው የነበሩት የባቡር ፉርጎዎቹ አስፈላጊ የቴክኒክ ፍተሻ ተደርጎላቸው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።
ይህም ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር በሎጂስቲክስ ዘርፉ እያበረከተ የሚገኘውን ሀገራዊ የባቡር ጭነት አገልግሎት ላይ ተደማሪ አቅም እንዲኖረው አድርጓል።
እያንዳንዳቸው ሰባ (70) ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሃያ (20) ሴንትራል ቢም ዋገኖቹ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ያለስራ ቆመው የነበሩ ናቸው፡፡
አሁን ወደ አገልግሎት በመግባታቸው ብረቶችን ጨምሮ ረዣዥም ጣውላዎችና መሠል ቁሳቁሶችን በፍጥነት፣ በተወዳዳሪ ዋጋና በከፍተኛ መጠን በማጓጓዝ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አይነተኛ ሚና መጫወት ጀምረዋል።
በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ከፍተኛ የወጪና ገቢ ዕቃዎቸ ጭነት በባቡር የማጓጓዝ አማራጭን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ ጎንዶላ ዋገኖችን (Gondola Wagons (CW 3 እና CW 4)) ወደ ሥራ መግባታቸው ይታወሳል።
ጎንዶላ ዋገኖቹ የመንግሥት ሸቀጦች የጉምሩክ ቁጥጥርን በመዳረሻ ጣቢያ እንዲያገኙ በማድረግ የተሳለጠ የባቡር ምልልስ እንዲኖር ማድረግ መቻሉን ኢዲአር በገጽ አጋርቷል።
sourece: www.motl.gov.et





Leave a Reply