አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሞሮኮ በወደብ፣ ተርሚናልና ሎጂስቲክስ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማሞ ምህረቱ የተመራ እና የኢትዮጵያ ባህርና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሮባ መገርሳንና ሌሎች የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ በሞሮኮ የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
ልኡካን ቡድኑ የሞሮኮ ወደብ፣ ተርሚናልና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱም ከሞሮኮ የወደብ፣ ተርሚናልና ሎጅስቲክስ ተቋም ሀላፊ መህዲ ታዚ ሪፊ ጋር በደረቅ ወደብ ልማትና አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፉን ለማሳደግ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረዋል።
ከውይይቱ መጠናቀቅ በኋላም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከሞሮኮው አቻ ተቋም ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በዘርፉ በትብብር መስራትና መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስን የሚያጠቃልል ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የባህርና ሎጀጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ስር የሚገኘውን የቃሊቲ ደረቅ ወደብና ተርሚናል የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የደረጃ ማሳደግን በጋራ መስራትን ያካተተ መሆኑን ከባህርና ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ድርጅት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
Some Useful links
Tags Cloud
There’s no content to show here yet.
Latest Posts
- የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ አፈፃፀም መሻሻል እንዳሳየ ተገለፀ::
- ኢትዮጵያ በብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ እምቅ አቅም እንዳላት ተገለፀ።
- የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከላኪዎች ፣ መርከብ ወኪሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በኮንቴኔራይዜሽን ዙሪያ ውይይቱ አደረገ።
- የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዲጂታል ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተሻለ ስራ አከናውኗል::
- የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ።