የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ 42 ኦፊሰሮችን አስመረቀ፤
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አካዳሚ የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ በኢንጂን እና በዴክ ኦፊሰርነት ያሰለጠናቸውን 42 ባሕረኞች በጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. አስመርቋል፡፡
ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም የተመረቁት ባሕረኞች የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠናዎችን በብቃት ያጠናቀቁ 18 የኢንጂን እና 24 የዴክ በአጠቃላይ 42 ኦፊሰሮች መሆናቸው ተገልጿል።
በምረቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
Source: EMA Telegram Channel Jan, 19 2024