September 5, 2024

ሚያዝያ 21፣2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከላኪዎች፣ መርከብ ወኪሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በኮንቴኔራይዜሽን ላይ ውይይት አድረገዋል።

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ተመስገን ይሁኔ ( የሎጅስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ፅ/ቤት ሀላፊ) እንደገለፁት:- የሚላኩ ዕቃዎችን በኮንቴኔር አሽጎ መላክ ከአንድ ኮንቴኔር 112.5 ዶላር ወጭን ማዳን እንደሚቻል፤ በባለሥልጣኑ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን መስራቱን፤ የመልቲ ሞዳል እና የዩኒ ሞዳል ሬሾን ፤ በዘርፉ የሚታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን እና ይህንን ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት የሚለውን አቅርበዋል።

በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ በተሳታፊዎቹ በኩል የተለያዩ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የኮንቴነር እጥረቱን ለመቀነስ ይረዳ ዘንድ  በኮንቴኔር ስርጭት በኩል የሚታዩ ክፍተቶችን፤ የመጣን ኮንቴነር ተመልሶ ለመጫን መጠቀም ቢቻል፤ የኤጀንቶችን አቅም ማሳደግ ቢቻል እና  ጁቡቲ ላይ የሚኖርን ዲሜሬጅ መቀነስ ቢቻል፤ የቀይ ባህር ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን እና ሌሎችም ሀሳቦችን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ዋና ዳይሬክተር አብዱል በር ሸምሱ (ኢንጅነር) በበኩላቸው:- ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ስለሆነ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እና ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ በባለሥልጣኑ በኩል መፈታት የሚችሉ ችግሮችን ለመፈታት ባለሥልጣኑ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም የትራንስፓርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እርስ በእርስ በመናበብ እና በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ እና ሁሉም የየድርሻውን ወስዶ ስራውን መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ቴሌግራም ግሩፕ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *