የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አመራርና ሰራተኞች የዘንድሮውን የዓለም ማሪታይም ቀን (World Maritime Day) በውይይት አከበሩ፡፡የዓለም የማሪታይም ቀን እ.ኤ.አ ከ1978 ጀምሮ መከበር የጀመረ ሲሆን በአባል ሀገራቱ ውሳኔ መሰረት በየዓመቱ መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ይከበራል፡፡ የዘንድሮው የዓለም የማሪታይም ቀን ‘’NEW TECHNOLOGIES FOR GREENER SHIPPING’’ በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ሲሆን ባለሥልጣን መ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ለሦስተኛ ጊዜ በውይይት አክብረዋል፡፡
በበዓሉ አከባባር ላይ ውይይቱን ያስጀመሩት የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር የኋላሸት ጀመረ እንዳሉት የበዓሉ ዓላማ የማሪታይም ዘርፍ ከ80 በመቶ በላይ የዓለምን የንግድ እንቅስቃሴ የሚያስተናድ በመሆኑ ለዓለም ኢኮኖሚ የሚኖረውን ፋይዳ ለማስተዋወቅ፣ በዘርፉ የሚሰሩ ባህረኞችንና ባለድርሻ አካላትን ለማመስገን እንዲሁም በዘርፉ የሚስተዋሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ወይም ተግዳሮቶች በማስታወስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ዘርፉን ለማዘመን የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣት እንዲችሉ ለማስገንዘብ ያለመ መሆኑን አብራርተው፤ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለዘርፉ ባለው ቀረቤታ በቀጣይ በበቂ ዝግጅት ዘርፉን ይበልጥ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል፡፡
ለውይይት መነሻ ያቀረቡት የማሪታይም አስተዳደር ተ/ዳይሬክተር ካፒቴን ጌትነት አባይ በበኩላቸው ለዓለም ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ድርሻ ያለው የማሪታይም ዘርፍ ይበልጥ በማስተዋወቅ አዳዲስ የተማሩ ወጣቶች ወደ ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ ለማድረግ፣ የመርከብ ኢንዱስትሪው ተመጣጣኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አጋዥ የሆነ፣ ምቹና ተስማሚ ለማድረግ በ2030 የተቀመጠውን ጎል ለማሳካት በዓለም የማሪታይም ድርጅት አባል ሀገራት እየተሰራ ያለውን ሥራ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በበኩሏ ከማሪታይም ዘርፍ የሚገኘውን ጥቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጅ መቀረጹ፣ የባህረኞች ማሰልጠኛ ተቋማትን በማቋቋም በሀገር ውስጥ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ፣ ባህረኞችን አሰልጥኖ በውጭ ሀገር የመርከብ ኩባንያዎች እዲቀጠሩ በማድረግ ሀገሪቷን የባህረኞች ሀገር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ፣ ሀገሪቷን የካርጎ እንቅስቃሴ እና የመርከብ ባለቤት ሀገር እንደመሆኗ መጠን የባህር ላይ የመርከብ ጉዞን በቴክኖሎጅ ለመቆጣጠርና የሎጅስቲክስ እቅስቃሴውን ለማሳለጥ የሚያስችል አዮሪስ (Ioris) ፕሮግራም መፈራረሟ፣ የሞጆ ደረቅ ወደብን ወደ አረንጓዴ የሎጅስተክስ ማዕከል ለማሸጋገር እየገነባች መሆኗ አበረታች ውጤት መገኘቱን ካፒቴን ጌትነት ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የዓለም ማሪታይም ቀን አከባበር አስፈላጊነትና ታሪካዊ ዳራ በማቅረብ፤ የዓለም ማሪታይም ድርጅት ዋና ፀሐፊ ያስተላለፉትን የቪዲዮ መልዕክት በማሳየት፤ የባህር ላይ ሥራ ለዓለም እድገት ያለው ትልቅ ድርሻ፣ የባህር ላይ ጉዞ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አስቸጋሪ፣ ውስብስብ፣ ያለ እረፍትና በብቁ የባህረኞች ሙያ የሚሰራ መሆኑን የዘርፉ ሙያተኞች ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን በበዓሉ ታዳሚዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ዘርፉን ለማዘመን፣ በማሪታይም እና ሎጅስቲክስ ሀገሪቷን ተጠቃሚ ለማድረግ የድርሻችንን መወጣት ይገባናል ብለዋል፡፡
Some Useful links
Totam elit laboris? Eu donec consectetuer litora adipisci praesent convallis augue
Tags Cloud
There’s no content to show here yet.
Latest Posts
- የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ አፈፃፀም መሻሻል እንዳሳየ ተገለፀ::
- ኢትዮጵያ በብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ እምቅ አቅም እንዳላት ተገለፀ።
- የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከላኪዎች ፣ መርከብ ወኪሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በኮንቴኔራይዜሽን ዙሪያ ውይይቱ አደረገ።
- የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዲጂታል ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተሻለ ስራ አከናውኗል::
- የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ።
Categories
- Africa (1)
- Blue Economy (1)
- Business (10)
- Construction (1)
- Culture (1)
- Event (6)
- Newsbeat (1)
- Project (2)
- Sports (1)
- Training (5)
- Uncategorized (6)
- World (4)