April 24, 2024
በሀገሪቱ የኤክስፖርት ጭነትን አሰባስቦና አቀናጅቶ መላክ (Consolidation) በሞጆ ደረቅ ወደብ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ይህንኑ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት የኤክስፖት ጭነትን አሰባስቦና አቀናጅቶ የመላክ ስራ መጀመሩ በወጪ ንግድ ለሚሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ውጪ ገበያ ምርቶቻቸውን ሲልኩ ኮንቴይነር እስኪሞላ በመጠበቅ ይወስድባቸው የነበረውን ጊዜ ይቆጥባል ብለዋል።

የተዘጋጁ ምርቶችቸውን አሰባስቦና አቀናጅቶ በመላክ በወቅቱና በፍጥነት ለደንበኞቻቸው ከማቅረብ ባሻገር እስከ 40 በመቶ የሚሆን ወጪ ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

በተበጣጠሰ ሁኔታና በከፍተኛ ወጪ በተሸከርካሪ ወደ ጅቡቲ ይጓጓዝ የነበረውን የኤክስፖርት ጭነት በማሰባሰብ፣ በኮንቴነር በማሸግና ባቡርን በመጠቀም ከምርት ቦታ እስከ ገበያ መዳረሻ ድረስ በተቀናጀ ሁኔታ የማጓጓዝ አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ በርካታ ጥቅም እያስገኘ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ ተግባር በሀገሪቱ እምብዛም ያልተለመደውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለማስተዋወቅና ለማጠናከር የሚስያችል ልምድ የሚያስገኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የሜርስክ (MAERSK) የምስራቅ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ካርል ሎሬንዝ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተመረቱ ምርቶችን ወደ አውሮፓና አሜሪካ ገበያ ለመላክ የተቀናጀ የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *