
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከአውሮፓ ህብረት እና ከዓለም አቀፍ ማሪታይም ድርጅት ጋር በመተባበር ለማሪታይም ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በዓለም አቀፍ የማሪታይም ሕግጋት ላይ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ የመርከብ ባለቤት ሀገር ከመሆኗም ባሻገር የዓለም አቀፍ የማሪታይም /የባህር ዘርፍ በመጠቀም ከ85 በመቶ በላይ ንግዷን የምታሳልጠው እና ባህረኞችን በማሰልጠን በዓለም የመርከብ ድርጅቶች እንዲሰማሩ በማድረግ ዘርፉ ለሀገራዊ እድገት የበኩሉን ሚና እንዲጫዎት በማድረግ ላይ በመሆኗ በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም አሟጦ ለመጠቀም ባለድርሻ አካላትን ማሰልጠንና የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን በስልጠናው ተብራርቷል፡፡