ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም.  (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን  ከኪንግደም ኦፍ ኔዘርላንድ ጋር በመተባበር ኩል ፖርት አዲስ በሚል ስያሜ  በሞጆ ለሚገነባው የቀዝቃዛ መጋዘንና ማጓጓዣ የአሠራር ሥርዓት  WAGENINGEN UNIVERSITY & RESEARCH በተባለ ተቋም በተጠና ጥናት ላይ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር አብዱልበር ሸምሱ፣ የኪንግደም  ኦፍ ኔዘርላንድ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር  Mrs Paula Schindeler  በተገኙበት በዘርፉ ባለድርሻ  አካላት ግምገማ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ  ማሪታይም  ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር  ኢ/ር አብዱልበር ሸምሱ  ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር  በሎጂስቲክስ ስትራቴጂው ከተጠቀሱት የመፍትሔ ሀሳቦች መካከል አንዱ  በቀላሉ የሚበላሹ የግብርና ምርቶችን ማቆያ የቀዝቃዛ መጋዘንና ማጓጓዣ የአሠራር ሥርዓት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው   በአርሶአደሩ የሚመረቱ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምረቶችን ሳይበላሹ  በአስተማማኝ ሁኔታ ለኤክስፖርት ለማቅረብ የቀዝቃዛ መጋዘንና ማጓጓዣ የአሠራር ሥርዓት በጥናት ተግባራዊ ማድረግ ማስፈለጉን ገልፀዋል፤
የኪንግደም ኦፍ ኔዘርላንድ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር  Mrs Paula Schindeler የኪንግደም ኦፍ ኔዘርላንድ መንግስት ከኢፌዲሪ መንግስት ጋር በትብብር በሎጂስቲክስ ዘርፍ ከሚሠራዎች ስራዎች አንዱ በቀላሉ የሚበላሹ የግብርና ምርቶችን ማቆያ የቀዝቃዛ መጋዘንና ማጓጓዣ የአሠራር ሥርዓት መሆኑንና ወደፊትም በትብብር እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

ጥናቱ ወደ ትገበራ ሲሸጋገር በቀላሉ የሚበላሹ የግብርና ምርቶችን ጥራታቸውን ጠብቀው በአስተማማኝ ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ገበያ የማጓጓዝ ሂደትን ውጤታማነት በመጨመር እና የሎጅስቲክስ ዋጋን በመቀነስ በሀገሪቱ የሎጅስቲክስ አሠራር ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ መሆኑ ተመላክቷል ፡፡

በመጨረሻም ከባለድርሻ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማጠቃለያ የሰጡት የሎጅስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ለማ የተሰጡ አስተያየቶችን አማካሪ ድርጅቱ በጥናቱ እንዲያካትት አቅጣጫ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

Source: EMA Official Telegram Group

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *