

ሚያዝያ 2/2017 ዓም(ትሎሚ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የሎጅስቲክስ (Logistics) እና አቅርቦ ት ሰንሰለት አስተዳደር (Supply Chain Management) የትምህርት እና ምርምር መርሀግብር የሚያካሂዱ ዩኒቨርስቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የዩኒቨርስቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ የማሪታይም ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ሺፒንግ እና ሎጅስቲክስ አመራሮች፤ የአዲስ አበባ፣ የጅማ ፣ ባህርዳር ፣ድሬዳዋ፣ ሰላሌ ፣ አርሲ እና ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚደንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ከኢትዮጵያ ጭነት አመላላሾችና ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዴንጌ ቦሩ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፋ ለሀገራችንን ኤኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን በፖሊሲ እና ስትራቴጂ ደግፎ በትኩረት መጠነ ሰፊ ስራ እየሰራ እና አበረታች ለውጦች እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Maritime Authority Official Telegram Group