ግንቦት 8፣2017 (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር መስፈርትን አሟልቶ በመገኘቱ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምስክር ወረቀት  ተሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ለመተግበር በተደረገ የኦዲት ስራ  መስፈርትን አሟልቶ በመገኘቱ የእውቅና የመስክር ወረቀት አግኝቷል። ወደዚህ ስርዓት ለመግባት በርካታ ስራዎች ስሰሩ መቆየቱን ያነሱት
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) ፣ እንደ ተቋም ይህን ሰርተፍኬት ማግኘ ተቋሙ  ለሚሰራቸው ዓለም አቀፍዊ ስራዎች እና በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ እንደሚያግዝና ለተቋም ግንባታ እጂግ ጠቃሚ ሲሆን፣ ግባችን የምስክር ወረቀት  ማግኘት ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ማሻሻያዎችን እያደረግን ቀጣይነት ባለው መልኩ አሰራርን ለማዘመን እጂግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

የምስክር ወረቀቱን ያበረከቱት የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት መዓዛ አበራ(ኢ/ር) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ይህንን ሲስተም ለመጠቀም መወሰኑ ተቋሙ የሚሰራቸው ስራዎች ዓለምአቀፍዊ ተቀባይነት እና  ተወዳዳሪ  እንዲሆን እንደሚያግዝ እንዲሁም በተቋም ውስጥ የአሰራር ግልፀኝነትን ለማምጣት ይረዳል ብለዋል። በቀጣይም ባለሥልጣኑ ሌሎች የISO የምስክር ወረቀት ለማግኘት ጠንክሮ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

Source: EMA’s Official Telegram Group

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *