
ታህሳስ 7፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሰለጠኑ ሴት ወጣት ኢትዮጵያውያን ክብር ዓለሙ ስሜ የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርዓት ተመርቀዋል።

የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብር ዓለሙ ስሜ( ዶ/ር) ተመራቂዎቹ ሁሉም ሴቶች መሆናቸው ለዘርፉ አዲስ ትርጉም እንደሚሰጥ እንዲሁም ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ በመሆኑ ስልጠናው የሙያ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ባህሎች ፣ቋንቋዎች እና እሴቶች የተገናኙበት ትንሿ ኢትዮጵያ የታየችበት መድረክ እንደነበር ገልፀው ለሁሉም ተመራቂዎች የስራ ዕድል እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦልጣፋ :-የኢትዮጵያ መንግስት ለሎጂስቲክስ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ከአምስት ዓመት በፊት ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂን በመንደፍ ሴክተሩን በተደራጀ አግባብ እየመራ እንደሚገኝ ገልፀው፤ ስትራቴጂው የሰው ሃብት ልማት ክፍተት ያመላከተ በመሆኑ የዛሬው የምረቃ ስነስርዓትም የዚሁ ስትራቴጂ አቅጣጫ እና ቅኝት መሆኑንም ገልፀዋል።
