December 6, 2024
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን 2ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወነ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ‹‹አሻራችን ለትውልዳችን›› መርሃ ግብርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አመራር እና ሰራተኞች ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታ አካባቢ 2ኛውና ማጠቃለያውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያብባል አዲስ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በባለስልጣን መ/ቤቱ ብቻ ለ2ኛ ጊዜና በማጠቃለያ የተካሄደ ችግኝ ተከላ መሆኑን በመጠቆም ችግኝ መትከል የጎርፍ አደጋን ለመከላከል፣ የሙቀት አማቂነትን በመቀነስ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው በተመሳሳይ መልኩ በወንዶገነት፣ በሎሜ ወረዳና በሞጆ አካባቢ ከተለያዩ መ/ቤቶች ጋር በመተባበር በርካታ ችግኞችን መትከል መቻሉን አስታውሰው፣ በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የባለሥልጣኑ እና የሞጆ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች፣ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር እና አማካሪ ድርጅት አመራርና ሰራተኞች ላደረጉት ተሳትፎ አመስግነዋል፡፡

በ2ኛው ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ 2ሺ ችግኞች መተከላቸውን እንዲሁም በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን፣ የፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ የሎጅስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽ/ቤት፣ የፕሮጀክቱ አማካሪና ኮንትራክተር አመራርና ሰራተኞች ተሳታፊ መሆናቸው የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ብርሃን ኪዳኔ ገልፀዋል፡፡

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስተባባሪው አቶ ደሳለኝ ጌታሁን ዝርዝር ገለፃ በማቅረብ ተሳታፊዎች እንዲጎበኙ የተደረገ ሲሆን የግንባታ ሥራው ከኮንትራክተርና አማካሪ ድርጅቱ ጋር በቅርበት በመመካከር በተሻለ ደረጃ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ በሞጆ ማዕከል ግንባታ መከናወኑ ለአረንጓዴ ሎጅስቲክስ የበኩሉን ሚና የሚያበረክት በመሆኑ ለመትከል የተደረገውን ርብርብ በመንከባከብ ሊደገም ይገባዋል፡፡

Some Useful links

Tags Cloud

There’s no content to show here yet.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *