October 28, 2024

ሕዳር 8/ 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለተቋሙ የግንዛቤ የማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት ስልጠናን ሰጥቷል። 
አብዱልበር ሸምሱ ( ኢንጂነር) በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት:- ይህ  መድረክ ለቋሚ ኮሚቴው አጠቃላይ ስለዘርፉ  ግንዛቤ አግኝተው  በምን ድጋፍ እናድርግ የሚለውን ለመለየት እንደሚረዳ ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ ስለተቋሙ አመሰራረት ፤ ስለተሰጠው ተግባር እና ሀላፊነት ፤ ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ፤ የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ እና የተቋሙ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ባለሥልጣኑ እንደዚህ አይነት ስልጠና በማዘጋጀቱ አመስግነው፤ ስለ ዘርፉ የተሻለ ለማወቅ እንደረዳቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመሰረተ ልማት እና ትራንስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ሸዊት ሻንካ፥ ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ይህንን ለማስቀጠል የሎጂስቲክስ ዘርፉን አቅም አማጦ መጠቀም አለብን ብለዋል። አያይዘውም ባለሥልጣኑም ዘርፉን ለማዘመን እየሰራው ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና በቋሚ ኮሚቴው በኩል የታዩ ማነቆዎችን ፈጥነን መፍትሔ በመስጠት የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት እንደ ምክር ቤት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

Source: EMA Telegram Channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *