January 15, 2025
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከኬንያ አቻው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና የኬንያ የወደብ ባለሥልጣን /Kenya Port Authority/ልዑካን ቡድን ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል በማሪታይም እና በሎጅስቲክስ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ዐበይት ስራዎች የቀረቡ ሲሆን፦ በማሪታይም ዘርፉ ባህረኞችን አሰልጥኖ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ረገድ እየተሰራ ያለውን ስራ፤ ሀገሪቱ ወደብ ሳይኖራት የመርከብ ባለቤት (Flag State) በመሆን ያገኘቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ፤ በሎጅስቲክስ ዘርፍ የታዩ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ለመፍታት የሚያስችል ብሔራዊ የሎጅስቲክስ ስትራቴጂ በመቅረፅ እና ተግባራዊ በማድረግ የተሄደበትን ርቀት እንዲሁም የመፍትሔ ሀሳቦቹ ምን ያክል ሎጅስቲክስን እያሳለጡ እንደሚገኙ ለልዑካኑ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የገቢ እና የወጭ ንግዷን ለማሳለጥ በሞምባሳ እና በላሙ ወደቦች መጠቀም እንደ አማራጭ እንድትይዘው በኬንያ ልኡካን በኩል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የኬንያ ወደቦችን በመጠቀም ረገድ በተለይም የሞምባሳ ወደብን በመጠቀም በሞያሌ ኮሪደር በኩል የእርዳታ እህልን የኬንያ ትራኮችን በመጠቀም እስከ አዳማ ማእከላዊ መጋዘኖች በማጓጓዘ ውጤታማ ስራ እንደተሰራ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

ኃላፊዎቹም አያይዘውም በቀጣይም ኮሪደሩን በቋሚነት ለመጠቀም የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን የጥናቱን ውጤት ታሳቢ በማድረግ ወደትግበራ እንዲሚገባ እና የወደብ አማራጭችን መጠቀም በመንግስት ትኩረት ተሰጦት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኬንያ ልኡካን ቡድን በበኩላቸው በተደረገላቸው ገለጻ እና ባገኙት ተሞክሮ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ሁለቱም ሀገራት በሚያስተሳስራቸው የሎጅስቲክስና ማሪታይም ዘርፍ በትብብር ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ አመርቂ ውይይቶችን ማካሄዳቸውን በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Some Useful links

Tags Cloud

There’s no content to show here yet.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *