September 5, 2024
መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በሚደረግለት ፕሮጀክት / Eu Crimario/ ከተባለው ኘሮጀክት ጋር በመተባበር በሁለት ዙር ስልጠና አሰልጥኗል።

መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በሚደረግለት ፕሮጀክት / Eu Crimario/ ከተባለው ኘሮጀክት ጋር በመተባበር በሁለት ዙር ስልጠና አሰልጥኗል። ኘሮጀክቱ በህንድ ውቅያኖስ እና አካባቢው ባሉ ሀገራት ላይ እና በቀይ ባህር ዙሪያ የሚገኙ ሀገራትን በማሪታይም ዘርፍ እና በማሪታይም ደህንነት እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ላይ የተሻለ ግንዛቤ የሚፈጥር ኘሮጀክት እንደሆነ አሰልጣኙ የክሪማሪዮ ባልደረባ አቶ ኤሊ ገልፀዋል።

የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከመስከረም 02 – 06 ቀን 2015 ዓ.ም መሰረታዊ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ ከመስከረም 09 – 13 ቀን 2015 ዓ.ም በከፍተኛ ደረጃ ተሰጥቷል።በዚህ ስልጠና መሰረታዊ የአዮሪስ ኘላት ፎርም ምንነት እና አጠቃቀም ፣ መረጃን ለመለዋወጥ ፣ መርከቦቹ የደረሱበትን እና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ እና የባህር ላይ ደህንነትን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል በስልጠናው ላይ ተዳሷል።

አዮሪስ/ Ioris/ ስሙ እንደሚያመለክተው በህንድ ውቅያኖስ እና አካባቢው የሚገኙ ሀገራት መረጃ የሚለዋወጡበት ፣ መርከቦችን የት እንዳሉ ለማወቅ የሚያግዝ ፣ የመርከቦችን ደህንነት ለማወቅ ብሎም የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ መረጃን በጥንቃቄ ለመለዋወጥ የሚረዳ ኘላት ፎርም ሲሆን ይህንን ፕላት ፎርም መጠቀም ለኢትዮጵያ ፍይዳው የጎላ እንደሆነ በስልጠናው በመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ኢንጅነር የኋላሸት ጀመረ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ገልፀዋል።


ኢንጅነር የኋላሸት ይህንን ስልጠና ላዘጋጁት እንዲሁም ለሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል። በስልጠናው ላይ ከኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን፣ ከኢትዮጵያ ባህር ሀይል እና ከፌደራል ፓሊስ ኢንተር ፓል የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ሀላፊዎች የስልጠናው ተሳታፊ ነበሩ።
በሁለቱም ዙር ለሰለጠኑ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ የሁሉም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ነበር። ሌላው ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን እና ለአሰልጣኙ ከኢትዮጵያ ባህር ሀይል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ስለኘላት ፎርሙ ሁሉም ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የማኔጅመንት አባላት ስለ አዮሪስ ምንነት እና አጠቃቀም በባለስልጣኑ የማሪታይም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ካፒቴን ጌትነት አባይ እና ከክሪማሪዮ በመጡት አቶ ኤሊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ካፒቴን ጌትነት አባይ / በባለሥልጣኑ የማሪታይም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / እንደገለፁት :- ለምን ይሄን ሲሰተም መጠቀም አስፈለገን ለሚለው ጥያቄ ይሄንን ኘላት ፎርም መጠቀማችን በቀይ ባህር እና አካባቢው ብሎም በዓለም ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ ፤ የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚረዳ ሲሆን ሌላው መረጃን ሴኩዩር በሆነ መንገድ ለመለዋወጥ እንደሚጠቅም ገልፀው ፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ይህንን ፕላት ፎርም ተግባራዊ ማድረጓ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ለማኔጅመቱ አብራርተዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የአዮሪስ ኘላት ፎርምን ለመጠቀም በተፈራረመው መሰረት ባለሥልጣኑ የአዮሪስ ኘላት ፎርምን በይፍ አስመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *