ታህሳስ 3፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ሁለተኛውን የሎጂስቲክስ  ማስተር ኘላን ጥናት በይፍ አስጀምሯል።

በጥናት ማስጀመርያ መርሃ ግብሩ ላይ ጥናቱን የሚያጠናው  አጥኝ  ድርጅት( ePtisa ) አጠቃላይ የጥናቱን ወሰን ፤ የሚያጋጥሙ ችግሮችን  እና  ጥናቱን ለመስራት የሚጠቀሙትን ስልቶች  እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት እና ከአሰሪው ድርጅት የሚጠበቁ ተግባራትንና ድጋፍ  አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣   በቀረበው ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ቢካተቱ እና ቢስተካከሉ የተባሉት ጉዳዮች ቀርበው ማብራሪያ  በአጥኝው ቡድኑ በኩል ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ፣ ሰፊና  ሀገራዊ  የሎጂስትክስ መሰረት ልማትና ስርዓትን እንዲሁም  አቅምና ክፍተቶቹን ምልዑ በሆነ መልኩ የሚመልስ ሲሆን አጥኝ ቡድኑ በትልቅ የሀላፊነት ስሜትና ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲፈጽሙ አሳስቧል። በሂደቱም ሁሉም ባለድረሻ አካላት ተገቢውን እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *