December 6, 2024
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ‹‹አሻራችን ለትውልዳችን›› መርሃ ግብርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አመራር እና ሰራተኞች ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ‹‹አሻራችን ለትውልዳችን›› መርሃ ግብርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አመራር እና ሰራተኞች ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ሁሉም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን፣ የፕሮጀክት ጽ/ቤቶች አመራርና ሰራተኞች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን 2ሺ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በበጀት ዓመቱ 6ሺ ችግኞችን ለመትከል በእቅድ የተያዘው አካል ነው።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ በኢንዱስትሪ ፖርኮች ያከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የሀገራዊ አረንጓዴ ሎጅስቲክስ ስትራቴጅ (Green Logistcs Strategy) አካል ሲሆን በበጀት ዓመቱ እየተከናወነ ባለው በሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አመራርና ሰራተኞች ለሶስተኛ ጊዜ መሳተፋቸው ታውቋል።

Some Useful links

There’s no content to show here yet.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *