About ETLP
ETLP/EMA Sep. 2018 ½
Paving the way for the future of Ethiopia’s Logistics!!!
The Ethiopia Trade Logistics Project (ETLP) – P156590 is established under the auspices of the Ethiopian Maritime Affairs Authority (EMAA). The objective of this Project is to enhance the performance of the Ethio-Djibouti corridor through improvements in operational capacity, efficiency, and range of logistics services at the Modjo Dry Port.
Modjo has been identified as which is the key node for the emerging Ethiopia’s intermodal trade logistics system because the railway becomes a key mode of transport for international trade along the Ethio-Djibouti corridor.
Hence, the project aims to supports the transformation of Modjo dry port into a multi-user facility Green Logistics Hub through investment that will meet the increasing demand for specialized value-added logistics services and increased export.
The project will achieve this through investments in physical infrastructure, ICT systems, and support for regulatory and institutional capacity support (Project administration, Monitoring & Evaluation and communication etc)
Vision of the Hub
Vision of the Hub is to transform Modjo dry port as Largest and best green logistics hub in Africa by 2025.
The project is financed by the World Bank (WB) with USD 150 million loans to be implemented over five years since its effectiveness, 7th July 2017. The project will be an integral element in achieving the Growth and Development Plan of Ethiopia.
ETLP/EMA Sep. 2018 2/2
The project is implemented by the Ministry of Transport (MoT) through the EMA. The Ethiopian Shipping and Logistics Services Enterprise (ESLSE) is the beneficiary of the project. This arrangement minimizes the degree of complexity and potential institutional overlap during implementation. Accordingly, project implementation unit (PIU) has been set up in the EMA responsible for the implementation of the project interventions and overall day-to-day project coordination and monitoring as well as communicating with the public and the stakeholders as required. The PIU has a team of experienced specialists and consultants to manage the implementation of the project.
The work of the PIU is to be directly overseen by the Director General of EMA and be guided and overseen by a Project Steering Committee (PSC). The PSC, chaired by the Ministry of Transport is comprise of representatives from the main government stakeholders (MoFEC, MoT, MoANR, MoPE, NBE, ERCA, and ERC, etc) and the main implementing and beneficiary agencies and other government agencies as deemed appropriate.
Project beneficiaries will primarily be private sector exporters, importers, manufacturers and farmers, those working for companies producing goods for export, government agencies involved in exporting and importing, and consumers.
___________________________________________________________________
መስከረም 2011 ማጉባ 1/3
የኢትዮጵያ ንግድ ልጂስቲክስ ፕሮጀክት
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ መንግስት ለትራንስፖርት ልማት በተሰጠው ትኩረት በመንገድ፣ በአቬዬሽንና አየር ትራንስፖርት፣ በባህር ትራንስፖርትና ማሪታይም አገልግልት አንዲሁም በቅርቡ ደግሞ በባቡር ትራንስፖርት ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል፡፡ የልጂስቲክስ ዘርፉን በሚመለከት ከሞጆ፤ ከሰመራ፤ ኮምቦልቻ፤ ከመቀላ፤ ከድሬዲዋ የደረቅ ወደቦች ልማት እንዲሁም የመንገድና ላልች መሰረተ ልማት ተከናውኗል፡፡
ምንም እንኳን እስከአሁን በተከናወኑ እንቅስቃሴዎች አበረታች ውጤቶች ለማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም የውጪ አማካሪዎቸን ጨምሮ በተለያዩ የዘርፉ አካላት በተካሄደ ጥናቶች እንደተረጋገጠው የልጅስቲክስ ዘርፉ አሁንም በሚፈለገዉ ደረጃ ያላደገና ዘመናዊ ባለመሆኑ ዘርፉ የአገሪቱን ዓለም አቀፍ የመወዲደር አቅምን እየጎዳዉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም መንግስት በንግድና ልጂስቲክስ ዘርፍ የታቀደ የወጪ ንግድና ኢንዲስትሪያላይዜሽን ግቦች ሉያስገኙ የሚችለትን የኢኮኖሚ ጠቀሜታ በመረዳት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘርፉን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን አፈጻጸም በተደራጀ አግባብ ለመፈጸም እና ወጥነት ያለዉ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንዲያስችለዉ የብሔራዊ ልጂስትክስ ስትራቴጂ በኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዲይ ባለስልጣን ተነድፎና በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ወደ ትግበራ ገብቶአል፡፡
የሞጆ ደረቅ ወደብ ከአገሪቱ የገቢ ንግድ 95% የሚደርሰዉን የወደብ አገልግልት የሚሰጥ ቢሆንም ያለው መሰረተ ልማትና የአገልግልት አሰጣጥ ከገቢ ንግድ መጠንና ከሀገሪቱ የኢኮኖሚዕድገት ጋር የተመጣጠነ ባለመሆኑ በአለፉት ዓመታት በኢትዮ-ጂቡቲ የንግድ ኮሪደር ሲፈጠር ለነበረዉ የተጓተተ የልጂስቲክስ ትራንዚት አፈጻጸም ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም በቀጣይም ችግሩን ለመፍታት የሚረዲ የአሰራር ስርዓት ካልተዘረጋና እና ሁለንተናዊ የተቋሙን አቅም ለማሳደግ ካልተቻለ ጉዲዩ ባገራችን የወጪ ንግድ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የገቢ ዕቃዎችን ኢኮኖሚያዊ በሆነ አግባብ በወቅቱ ለተጠቃሚዉ በማድረስ ረገድ የሚያስከለዉን ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ ሥለዚህም በመረዳት የሞጆ ደረቅ ወደብን ሁለንተናዊ የልጂስቲክስ አቅምና አፈጻጸም ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ዓላማ ለማሳካት እንዲቻል በዓለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡
በመሆኑም ከዓለም ባንክ ጋር ለንግድ ልጂስቲክስ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ110,400,000 (አንድ መቶ አስር ሚሉዮን አራት መቶ ሺህ) ዩ ኤስ ዲ ወይም 150,000,000 (መቶ ሃምሳ ሚሉዮን) የአሜሪካን ድላር የብድር ስምምነት መጋቢት 29/2009 ዓ.ም (April 07/2017) ተፈርሟል፡፡ ፕሮጀክቱም እ.ኤ.አ ከጁላይ 5 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡
መስከረም 2011 ማጉባ 2/3
የፕሮጀክቱ ዓላማ
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዓላማ የሞጆ ደረቅ ወደብ የማስተናገድ አቅም፣ ቅልጥፍና እና ተዛማ የልጂስቲክሰ አገልግልቶችን ደረጃ ከመሰረቱ መቀየር እና የኢትዮ-ጂቡቲን የንግድ ኮሪደር /መተላለፊ አቅም የአገሪቱ የኢኮኖሚዉ ዕድገት በደረሰበት ደረጃ መሸከም እንዲችል ማብቃት ነዉ፡፡
ፕሮጀክቱ የሚያካትታቸዉ ተግባራት፡
በፕሮጀክቱ የተካተቱት ሶስት ዋና ተግባራት የሚከተለት ናቸው
ሀ) በሞጆ ያለውን መሰረተ-ልማት ማሻሻል (120ሚ. ድላር)
- በዚህ የፕሮጀክት ክፍል ሞጆን ወደ ላቀ የልጂስቲክስ ማዕከል (A LOGISTICS HUB) ለመቀየር ለማሳደግ የሚከተሉት ኢንቨስትመንቶች ይከናወናለ፡፡
የኢንተርሞዲል ማመላለሻ ፋሲሉቲ፡- የእቃ ጭነቶችን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ባቡር እንዲሁም ወደ መዲረሻ/መነሻ የሚኖረውን ደርሶ መልስ ፈጣን በሆነ ሂደት ለማሳለጥ የሚያግዙ የክሮስ ድኪንግ፣ የክሬንና የመሳሰለት ፋሲሉቶችን ግዢ ለማከናወን ድጋፍ ይደረጋል፡ - የኮንቴነር ጭነት ማስተናገጃ ቦታና የቁስ አቅርቦት፡- የኮንቴነር ጭነት ማስተናገጃ ቦታውን ለማስፋፋት፣ አጋዥ የማቆያ ቦታዎችንና የቢሮ ህንጻዎች ለመገንባት የሚደረጉ የሲቪል ስራዎች እንዲከናወኑ ድጋፍ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ለተለያዩ ማሽኖች ግዢና የዩቲሉቲ አቅርቦቶች ድጋፍ ይከናወናል፡፡
- የኮንቴነር ጭነት የማስተናገጃ ጣቢያ፡- ከውጪ የሚገቡትን ኮንቴነሮች ለይቶ ለማውጣትና ወደ ውጪ የሚላኩት ደግሞ አሽጎ ለመላክ የሚያስፈልጉ ፋሲሉቲዎች ግዢ ይከናወናል፡፡
- የደረቅ እቃዎች ማከማቻ መጋዘንና የባጂንግ ፋሲሉቲ፡- የደረቅ እቃ ጭነቶችን በተሻሻለ ሁኔታ ለማቆየት የሚያስችል መጋዘንና ለመለየት የሚያስችል ፋሲሉቲዎች ግዢ ለማከናወን ድጋፍ ይደረጋል፡፡
- የጥቅልና የተያያዥ ጭነቶች ማቆያ:- እቃዎችን ከኮንቴነር ለማስወጣት የሚያግዝና ለእቃዎች ማቆያ የሚሆን ዘመናዊ የጭነቶች ማስተናገጃ ፋሲሉቲ ይገነባል፡፡
ለ) የኢንፎርሜሽን ቴክኖልጂ ስርዓቶችን በማጠንከር የተቀናጀ አሰራር እንዲኖር ማድረግ (15ሚ. ድላር) በዚህ የፕሮጀክቱ ክፍል የሞጆ የደረቅ ወደብ አገልግልት አሰጣጥ እንዲጠናከርና በባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ አሰራር እንዲኖር የሚያግዙ ስራዎች ይከናወናለ፡፡ እነዚህም በተቆጣጣሪ መ/ቤቶች መካከል ከልጂስቲክስ ስርዓቱ ጎን ለጎን የሚኖርን የኤላክትሮኒክ መረጃ ትስስር የሚያጠናክር ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖልጂን መሰረት ያደረገ የመረጃ አያያዝ ልማት ለመዘርጋት የሚያስችል የሶፍትዌርና ሃርድዌሮች ግዢ ለማከናወን ድጋፍ ይደረጋል፡፡
መስከረም 2011 ማጉባ 3/3
ከወደቡ ወይም ከተርሚናልች ወደ ውስጥና ውጪ የሚገቡ የተለያዩ ካርጎዎች በሚመለከት የአገልግልት አሰጣጡን ለማሳለጥና ለቁጥጥር እንዲረዲ በሞጆ የደረቅ ወደብ ዘመናዊ የተርሚናል ኦፕሬሽ ሲስተም እና የኤላክትሮኒክ ቁጥጥር ማካሄጃ የፍተሻ ማሽን እንዲገነቡ ድጋፍ ይደረጋል፡፡
ሐ) የአስተዲደራዊ እና ተቋማዊ (አቅም ግንባታ)ድጋፍ (15ሚ. ድላር)
በዚህ ክፍል፡
- ፕሮጀክቱን በብቃት ለማስፈጸምና የሞጆ ወደብ ዘርፈ ብዙ አገልግልትን በማዘመን ረገድና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የተሻለ ለመስራት የሚያስችሉ ጥናቶች፣ ነባራዊ የፖሉሲና የቁጥጥር ማዕቀፎች ትንተናዎች፣ የአዋጭነት (ፊዝቢሉቲ) ጥናቶችና ወዘተ በማድረግ ባለድርሻ አካላት በተለይም የማሪታይም ጉዲዮች ባለስልጣን፣ የልጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ እና ብሄራዊ ልጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ካውንስል የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይደረጋል፡፡
- ለፕሮጀክት አስተዲደር፣ የአካባቢና የማህበረሰባዊ ጥበቃ ስራዎች፣ የባለድርሻ አካላትንና ህብረተሰቡ ግንኙነት ስራዎች፣ ክትትልና ግምገማ፣ የአቅም ግንባታ እና በውጪና በሀገር ውስጥ አማካሪዎች የሚከናወኑ የተለያዩ ጥናቶች ወጪ ይሸፈናል፡፡
የብድር ስምምነቱ ዋና ዋና ገፅታዎች:-
የ110,400,000 (አንድ መቶ አስር ሚሉዮን አራት መቶ ሺህ) ኤስ ዲ አር ወይም 150,000,000 (መቶ ሃምሳ ሚሉዮን) የአሜሪካን ድላር ከወለድ ነፃ ሲሆን
- የ6 ዓመታት የችሮታን ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ፣
- ባንኩ በሚወስነው መሰረት ጥቅም ላይ ባልዋለው የብድር ገንዘብ ላይ በአመት እስከ 0.5% የሚደርስ የግዳታ ክፍያ ሊከፈልበት ይችላል፤
- ባንኩ የብድሩን ገንዘብ በማስተዲደር ረገድ ለሚሰጠው አገልግልት ጥቅም ላይ በዋለውና ባልተከፈለው የብድሩ ገንዘብ ላይ በአመት 0.75% የአገልግልት ክፍያ ይከፈልበታል፡፡
ማጠቃለያ
ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም ከዓለም ባንክ በብድር የተገኘው ገንዘብ የአገራችንን የልማት እድገት ለማፋጠን ቁልፍ ሚና የሚኖረው ሲሆን የሃገሪቱን የንግድ ዋጋ በመቀነስ፤ ለኢንዲስትሪያላይዜሽን ዕድገት እንዲሁም አገራችንን የኤክስፖርት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪ ብድሩ ከወለድ ነፃ በመሆኑ ከሀገራችን የብድር አስተዲደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም ነው፡፡