
ታህሳስ 18፣2018ዓ.ም (ኢማባ) ሁለተኛው ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2025 አውደ ርዕይ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ተመስገን ጥሩነህ እና የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተከበሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር ) በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት ተከፍቷል።

በአውደ ርዕይው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፤ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት እና የተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

የትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ይህ አውደ ርዕይ እና ፎረም ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 22፣2018 ዓ.ም ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።