ታህሳስ 15፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረቸ ልማት እና የትራንስፓርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋሙን የስራ አፍጻጻም በመገምገም  የሞጆ አረንጓዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባተን ጎብኝተዋል።

በጎብኝቱ ወቅቱ የተቋሙ የስራ አፍጻጻም ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን፣ ከአሁን ቀደም የተሰጡ ግብረ መልሶች ላይ የተሻለ ክንውኑ መኖሩን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል። በተመሳሳይ  የሞጆ አረንጓዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባታ ያለበትን ሁኔታ  ተዘዋውረው  የተመለከቱ ሲሆን ኘሮጀክቱ  ያለበት አፈጻጻም ጥሩ መሆኑን አንስቷል። ከፕሮጀክቱ ጎን ለጎን በስፍራው ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፍት ስራዎችን እና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችንም ተመልክተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሰቢ  የተከበሩ ኘሮፌሰር  መሐመድ አብዱ እንደገለፁት በጉብኝቱ ወቅት የተመለከቱት ነገር አበረታች መሆኑን  ገልፀው በተለይ  የሞጆ አረንጓዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባታ አሁን ያለበት ደረጃ  ለሌሎች ኘሮጀክቶችም ምሳሌ መሆን የሚችል  እንደሆነ የገለፁ ሲሆን መሰረተ ልማቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርብ ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ስለኘሮጀክቱ እና አጠቃላይ የተቋሙን አፈጸጸም ላይ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራርያ የሰጡ ሲሆን  ቋሚ ኮሚቴው ለተቋሙ  በቅርበት ለሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል አመሰግነው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *