ታህሳስ 10፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ፓርት ኮሚኒቲ ሲሰተምን(Ethiopian port community System) ለማበልፀግ የሚያስችል ስምምነት በዘርፉ ከተሰማራ ድርጅት ጋር   በመፈራረም ወደ ስራ ገብቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሲሰተሙን የሚያለሙት ድርጅቶች በታቀደው ጥራትና ጊዜ ለማድረስ የሚያስችላቸውን ዝግጅት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በቀረበው ሪፖርት  ላይ በተሳታፊዎቹ በኩል   ቢካተቱ እና ቢስተካከሉ ተብለው የተነሱ ጉዳዮች ቀርበው ማብራሪያ  ተሰጥቶበታል። ሲሰተሙ በዋናነት በደረቅ ወደብና አጠቃላይ በንግድ ሎጂስቲክስ ላይ የሚሰሩ ተቆጣጠሪ የመንግሰት ተቋማትንና ሌሎችን ባላድርሻ አካላትን በመረጃ ልውውጥ ለማስተሳስር ታሲቦ የሚሰራ ሲሆን የዘርፉን ቅልጥፍና እንደሚያሻሽል የታመነበት ነው። በዚሁ አግባብ አልሚው ድርጅት  ስራውን አጠናቆ በተያዘለት ጊዜ እንዲያስረክብና በዚህ ሂደት የሚሳተፉ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ምክትል ዋና/ደይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *