ህዳር 08 ፣2018 ዓ.ም (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኢ/ር አብዱልበር ሸምሱ   የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አመራር እና ሰራተኞች የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣንን ከመጋቢት 2015 ዓ.ም  እስከ ጥቅምት 03/ 2018 በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር)  የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና  ሎጂሥቲክስ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ሎጂስቲክስን ትራንስፎርም  በማድረግ ሂደት እንዲሁም  የሞጆ ደረቅ ወደብ የአረንጓዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል መሰረተ ልማት ከነበረበት ችግሮች በማላቀቅ ለመጨረሻው  ምዕራፍ እንዲደርስ ለሰጡት የአመራር ብቃት እንዲሁም  ተቋሙ ይመሩ በነበረበት ወቅት ለሰሯቸው ሰው ተኮር ስራዎች የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር አድርገውላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *