የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በሀገራችን ለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ የአስቻይነት ሚናውን በሚገባ መወጣቱን ገልፀዋል።

የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ መቅደስ ዳባ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን ጠቁመው በቀጣይም ከዚህ የተሻለ እድገት እንደሚመዘገብ በርካታ አመላካች ሁኔታዎችች መኖራቸውን ገለልፀዋል።

ይህ አመርቂ የኢኮኖሚ እድገት ሊመዘገብ የቻለውም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉ የአስቻይነት ሚናውን በሚገባ መወጣት ስለቻለ ነው ብለዋል።

የወጪና ገቢ ምርትና የሀገር ውስጥ የጭነት እንቅስቃሴ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ በዚሁ ልክ ራሱን ከማሳደግ በተጨማሪ እንደ አንድ የኢኮኖሚ ሴክተር የበለጠ ሊሰራ እንደሚገባ አክለው ገልፀዋል።

ትሎሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *