January 14, 2025
እንደ ተቋም አሁን ያለንበት ወቅት በርካታ ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወደ እኛ የሚመጡበት ሰዓት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ለተጨማሪ ስራ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል::

ታህሳስ 26/2016 ዓ.ም (ኢማባ) የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በመርከብ ወኪልነትና መልቲሞዳል ትራንስፖርት ስርዓት፤ በዕቃዎች አስተላላፊነት፤ በመርከብና ወደብ ደህንነት፤በወደብ አከናዋኝነት ሂደቶች፤ በአደገኛ ዕቃዎች ጭነት ላይ ዓለም አቀፍ የማሪታይም አሰራር እና በዓለም አቀፍ የመርከብና የባህር ትራንስፖርት ላይ ሲከታተሉት የነበረውን ስልጠና አጠናቀዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ ከሰሞኑ ከወደብ ጋር ተያይዞ ከተሰማው የብስራት ዜና ጀምሮ በርካታ ተደራራቢ ሀላፊነቶች ወደ እኛ የሚመጡበት ሰዓት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ለተጨማሪ ስራ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
ስልጠናው የዝግጂቱ አንድ አካል መሆኑን የገለጹት አቶ ፍራኦል ስራዎችን በዕውቀትና ክህሎት ለመከወንና ለመምራት የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
የሀገራችንን የሎጅስቲክስ ሴክተር አሁን ያሉበትን ድክመቶች ተረድቶ ማረም እንደሚገባ አስረድተው ስራዎችን በጊዜና በጥራት ማከናወን ለነገ የማይባል ተግባር እንደሆነም ም/ል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው በብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በዛሬው ዕለት በስኬት ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *