April 23, 2024

የሀገራችንን የሎጀስቲክ ዘርፍ ለዉጥ ለመፍጠር እንዲያግዝ በፀደቀዉ የብሄራዊ ሎጀስቲክ ስትራቴጂ መሰረት ዘርፉን ለግል ኩባንያዎች ክፍት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ የህንንም ተከትሎ የመልቲ ሞዳል ትራንሰፖርተ አከናዋኝ የንግድ ስራ ፈቃድ እና ብቃትን ለማረጋገጥ የሚያስችለዉ መመርያ ቁጥር 802/2013 በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ፀድቆ ወደ ስራ ገብቶአል፡፡

መመርያዉ በፎብ ስርዓት የሚገደዱ ገቢ እቃዎች እና በፎብ የግዢ ስርዓት የማይገደዱ ገቢ እቃዎችን ለማስተናገድ የሚችሉ የመልቲሞዳል አከናዋኞች ብቃት ለማረጋገጥ እና ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝርዝር መስፈርቶች በማካተት የተዘጋጀ ነዉ፡፡

በፎብ የግዢ ስርዓት ለሚገደዱ ገቢ ዕቃዎች የመልቲ ሞዳል ትራንፖርት አከናዋኝ ሆነዉ ወደ ዘርፉ እንዲገቡ የሚጠበቁ አካናዋኞች በስራ ላይ ያለዉን የመልቲሞዳል ኦፕሬተር ጨምሮ ቁጥራቸዉ ከአምስት ያልበለጡ መሆን እንዳለበት ተወስኖአል፡፡

በዚህም መሰረት በፎብ የግዢ ስርዓት ለሚገደዱ ገቢ ዕቃዎች የመልቲሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ለሚፈልጉ ድርጅቶች ባለስልጣን መ/ቤቱ በመመርያ ቁጥር 802/2013 አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀፅ 10 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ለዘርፉ ሥራ ብቃት ያላችዉን ኩባንያዎች አወዳድሮ የሥራ ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ  ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 60 (ስልሳ) ቀናት ዉስጥ በባለስልጣን መ/ቤቱ 9ኛ ፎቅ የሎጀስቲክ አስተዳደር ቢሮ በመገኘት እንድተመዘገቡ እና ዝርዝር የመመልመያ መስፈርቶችንና መመርያዉን በመዉሰድ ብቃታችሁን የሚያረጋግጥ ሰነድ በተጠቀሰዉ ጊዜ ዉስጥ እንድታቀርቡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

አድራሻ፡ ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ማሪዮት ኤክስኪዬቲቭ አፓርትመንት ጎን ሰንሻይን ቁጥር 4 ህንፃ  9 ወለል ሲሆን፤

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር  0115156468/0912005392 አቶ ያለዉ ተስፋዬን  ወይም 0115548209/0949737669 አቶ መንግስቱ አለኸኝ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *