January 14, 2025

ኢትዮጵያ በብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ያልተነካ እምቅ አቅም እንዳላት ይህንንም ለመጠቀም የብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስትራቴጂውን ለማስፈፀም የሚረዳ የድርጊት  መርሃ ግብሩን ባለድርሻ አካላት ነሐሴ 01/2016ዓ.ም ገምግመዋል።
መድረኩን ኢጋድ፣ የአውሮፓ ህብረት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን በመተባበር አዘጋጅተውታል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልበር ሸምሱ (ኢንጅነር) እንደገለፁት:- ኢትዮጵያ በብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ያልተነካ እምቅ አቅም እንዳላት እና እሱን ለመጠቀም ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዚህ መድረክ ኢጋድ  በቀጠናው ሀገራት  የብሉ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ ያለውን  ተግባራት  እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሉ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ( ከ2023- 2027) የቀረበ ሲሆን ስትራቴጂውን ለመተግበር የሚረዳ የድርጊት መርሃ ግብር እና  የብሉ ኢኮኖሚ  ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ስነ ምህዳራዊ ፋይዳውን  በዝርዝር ቀርቧል።

የብሉ ኢኮኖሚ ለኢትዮጵያ  ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋፆ፤በስራ ዕድል ፈጠራ ፤ ለሀገሪቱ GDP  የሚዋጣውን ድርሻ  እና ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራበት ከዚህም በላይ ሊያበረክት እንደሚችል ዶ/ር አስያ ማስኬቭ በአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ አማካሪ ገልፀዋል።
በቀረበው የድርጊት መርሃ ግብር ላይ መካተት አለባቸው የሚሏቸውን ሀሳቦች በተሳታፊዎቹ በኩል ቀርበዋል።

በመጨረሻም ኢጋድ ኢትዮጵያ ከብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው  የኢትዮጵያ መንግስት ብሎም የሚመሩት ተቋም  በብሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ  ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ  እንደሆን ገልፀዋል።

Source: Ethiopian Maritime Authority Official telegram page

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *