January 16, 2025

በአገር ዓቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ የሀገር ውስጥ ውሀ ትራንስፖርት የደህንነት መመሪያ በማዘጋጀት የጉዞ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የትራንስፖርት አገልግሎቱ ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ይህ ረቂቅ መመሪያ እንዲዘጋጅ ሆኗል፡፡

በመሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች ፣የትራንስፖርት አከናዋኞች ፣አገልግሎት ተጠቃሚዎች እና የሚመለከታችሁ የፌዴራል፣የክልል ባለድርሻ አካላት  እና  የህብረተሰብ ክፍሎች የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ እንዲዳብርና ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ጠቃሚ ግብዓቶች፣አስተያቶችና ማንኛውም ይጠቅማሉ የምትሏቸውን  ገንቢ  መረጃዎች በመለገስ የዜግነት ድርሻችሁን  እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡

የሚሰጡት ግዓብያቶች፣አስተያየቶች በድረ-ገፁ ላይ በሚፃፍ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ዋና መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን ፍለፊት  በሰን ሻይን ህንፃ 8ኛ ፎቅ በአካል መጥቶ ገንቢ አስተያየቶች መስጠት ይቻላል፡፡ ለምትሰጡን አስተያየቶችና ግብዓቶች   በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *